አቶ ተፈራ ዋልዋ ዓለም አቀፍ እውቅና ተሰጣቸው
አቶ ተፈራ ዋልዋ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ እና አሁን ላለበት ደረጃ እንዲደርስ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዓለም አቀፍ እውቅና ተሰጣቸው፡፡
ዓለም አቀፉ የአስትሮኖሚ ህብረት ጠቅላላ ጉባዔውን በኦስትሪያ ቬና ሲያካሂድ ነው አቶ ተፈራ ዋልዋን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና የሰጣቸው፡፡ አቶ ተፈራ ዋልዋ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ማህበርን በበጎ ፈቃደኝነት መስርተው ከማገልገል ጀምሮ አሁን የማህበሩ የበላይ ጠባቂ በመሆን እያለገሉ ነው፡፡